ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ

Date:

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን #ውድድር 56 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዳግም አሻሽሏል።

​ዮሚፍ ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በሊዝበን ያስመዘገበውን የ57 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ የቀድሞ ክብረ ወሰን በ29 ሰከንዶች አሻሽሏል።

ዮሚፍ እ.አ.አ. በ2024 ቫሌንሲያ ላይ 57 ደቂቃ ከ30 ሰኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቱ በዓለም የግማሽ ማራቶን ንግስናውን በድጋሚ አረጋግጧል።

​በተመሳሳይ በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፎይተን ተስፋይ ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ57 ሰኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።

የዮሚፍ አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰን የዓለም አትሌቲክስን ይፋዊ ማረጋገጫ የሚጠብቅ ይሆናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...