የ52ኛው የበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድር አሸናፊ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ወደ አገሯ ስትመለስ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር አቀባበል ተደረገላት።
አትሌቷ በውድድሩ 2 ሰዓት፣ 11 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት የድል አክሊሉን የተቀዳጀች ሲሆን፣ የበርሊን ማራቶንን ለሦስተኛ ጊዜ በማሸነፍ ልዩ ስኬት አስመዝግባለች።
ትዕግሥት አሰፋ አዲስ አበባ ስትደርስ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች በአየር ማረፊያው ተገኝተው የክብር አቀባበል አድርገውላታል።
የአትሌቷ ድል የኢትዮጵያን የረጅም ርቀት ሩጫ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በድጋሚ ያሳየ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድሮች ያላትን ብቃትና ተከታታይ ድል አረጋግጣለች።
