የአስቸኳይ ጊዜ እወጃ ስርአት ለመዘርጋትና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ

Date:

በኢትዮጵያ ቅጽበታዊ አደጋ ሲከሰት እና ከአቅም በላይ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ እወጃ ስርአት ለመዘርጋትና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ምክክር እንደተደረገበት ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን ከአስቸኳይ ግዜ እወጃ ስርአት ከመዘርጋት እና ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ ተግባራትነ ያቀፈ ነው ተብሏል።

የሰብአዊ ድጋፍ፣ የዘላቂ ልማት እና የሰላም ግንባታ እቅዶችን ለማስተሳሰር የሚያስችል የተሟላ የህግ ማዕቀፍ ለመዘርጋት እንዲያስችል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ መሆኑ ተገልጿል፤ ፤ በሚሉ ድምጽ ለቋሚ ኮሚቴው ለዝርዝር እይታ ተልኳል።

የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የቅድመ አደጋ፣ የአደጋ ወቅትና ድህረ አደጋ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የፌደራልና የክልል አስተዳደር ተቋማት የውስጥ አቅም ለመገንባት ያስችሏልም ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክር ቤት መቋቋምን የተመለከቱ ድንጋጌዎች እና ስለ ኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት የምክር ቤቱ ስልጣንና ተግባራት ዝርዝር መረጃ መያዙ ተጠቁሟል።

ስለፌደራል መሪ ዘርፍ ተቋማት እና የክልል መንግስታት ተግባርና ኃላፊነት፣ ስለአደጋ ተጋላጮችና ተጎጂዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ መቋቋም የሚመለከቱና ሌሎች ድንጋጌዎች መካተታቸውም ታውቋል።

የምክር ቤት አባላትም አዋጁ የሚደረጉ ድጋፎች በተቀናጀ መልኩ እንዲደረጉና ለተጎጂዎች እኩል ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ከእርዳታ ጠባቂነት በመላቀቅ እራስን ለመቻል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 16/2017 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...

“ሎዛ ዘፀአት”እና “የሎዛ ድርሳናት”ተከታታይ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍት ተመረቁ

በጋዜጠኛና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ የተጻፉት ሎዛ ዘፀአት(2014 ዓ.ም) እና...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት...

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...