ባለፉት 10 ወራት በተደረገ የቁጥጥር ስራ 98 የጤና ተቋማት፣ 1መቶ5 የመድኃኒት ችርቻሮ ተቋማት እንዲሁም 9መቶ40 የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
እርምጃ ከተወሰደባቸው 1ሺ1መቶ43 ተቋማት፤ 9መቶ16የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣2መቶ20 በጊዜያዊነት የታሸጉ እና 7ተቋማት ብቃት የተሰረዘባቸው መሆናቸውን በባለስልጣኑ የምግብ እና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ስራ ላይ በተሰሩ ስራዎች ከ1መቶ42 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ምርቶች መወገዳቸውንም ገልፀዋል ።
የመጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ፣ ህገወጥ እርድ ፣ የምግብ ክለሳ እና መሰል ህገወጥ ተግባራት በቁጥጥር ሂደት መገኘታቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ከቁጥጥር ስራው ባሻገር ባለፉት አስር ወራት ከ21 ሺ ለሚበልጡ የጤና ተቋማት፣ የባህል ህክምና ተቋማት፣ ለመድኃኒት ችርቻሮ ተቋማት እና ለጤና ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ መሰጠቱን ጠቅሰዋል ።
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ እስጢፋኖስ ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
