ፍሬሕይወት ታምሩ የአፍሪካን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ፤ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ 100 ሴቶች መካከል አንዷ በመሆን አህጉራዊ እውቅና አግኝተዋል።
«አፍሪካ ሃይፐርስኬለርስ» እና «ዘ ሊትልስቴፕስ ግሩፕ» በጋራ ባወጡት በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተመረጡት፣ ኢትዮ ቴሌኮምን በብቃት በመምራት፣ ኔትወርክን በማስፋፋት እና «ቴሌብርን» በማስተዋወቅ ለሀገራችን የዲጂታል ሽግግር ትልቅ መሰረት በመጣላቸው ነው።
በዚህ አህጉራዊ ዝርዝር ውስጥ ከእሳቸው ጋር የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ገጽታ እየቀየሩ ያሉ እንደ ናይጄሪያዋ የ«ማይንዋን» መስራች ፋንኬ ኦፔኬ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሴት መሪዎች ተካተዋል።
