ዛሬ ህዳር 12 ቀን ነው። “ህዳር ሲታጠን” በሚል ቆሻሻን ሰብስቦ የማቃጠል ልማድ ተገቢ አለመኾኑንና የሚያስቀጣ ድርጊት መኾኑን የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሰሞኑን አስታውቋል።
ህዳር ሲታጠን በኢትዮጵያ በ1911 ዓ.ም. በህዳር ወር (ህዳር 12) በተከሰተው የስፓኒሽ ፍሉ (“የህዳር በሽታ” ወይም “የባቡር በሽታ”) ወረርሽኝ ምክንያት የተጀመረ ልማድ ሲሆን፣ በሽታውን ለመከላከል በየደጁ ቆሻሻና አሮጌ ዕቃዎችን የማቃጠል እንዲሁም የጽዳት ዘመቻ የማካሄድ ትውፊት ነው።
ቆሻሻን ከማቃጠል ይልቅ በአግባቡ ማስወገድ፣ መልሶ መጠቀም እና አካባቢን በጽዳት ዘመቻ ማጽዳት ለጤናና ለከተማ አየር የተሻለ መኾኑ ይታመናል።
