ኤአይ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት ዕድሉ ከ10 በመቶ በላይ ነው ተባለ

Date:

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ የሚችልበት ዕድል ከ10 በመቶ በላይ እንደሆነ የኤአይ ደኅንነት ተመራማሪ አስጠንቅቋል።

የአንትሮፒክ ተቋም ከፍተኛ የኤአይ ደኅንነት ተመራማሪ ኢቫን ሁቢንገር በማሕበራዊ ሚዲያ ኤክስ ባወጣው ጽሑፍ፣ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ኤአይ የሰው ልጅን በሙሉ ሊያጠፋ የሚችልበት ዕድል ከ10 በመቶ በላይ እንደሚገመት ገልጿል።

የተመራማሪው ማስጠንቀቂያ የኤአይ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እያደገ በመሆኑና ከዚህ ጋር ተያይዘው ሊፈጠሩ የሚችሉ ከባድ አደጋዎች ላይ በቂ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያሳስብ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...