ሕገወጥ የማዕድን ንግድንና ኮንትሮባንድን ለመግታት በአየር ትራንስፖርት ማጓጓዝ ላይ ገደብ ተጣለ

Date:

የማዕድን ሚኒስቴር ሕገወጥ የማዕድን ንግድንና ኮንትሮባንድን ለመግታት በሚል በአገሪቱ ውስጥ የማዕድን ምርቶችን በአየር ትራንስፖርት ማጓጓዝ ላይ ገደብ መጣሉን አስታውቋል።

ገደቡ የመጣው በሲቪል አቪዬሽን ዋና ደህንነት መምሪያ አማካኝነት ሲሆን፣ ከክልሎች በአውሮፕላን ተጭኖ ወደ መሀል አገር የሚመጣ ማዕድን አቅጣጫ ቀይሮ በኮንትሮባንድ እንዳይወጣ ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በማዕድን ሚኒስቴር የማዕድናት ግብይት መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢዮብ በቀለ (ዶ/ር) እንዳብራሩት፣ ይህ አሰራር ከተጀመረ በኋላ ሕጋዊ ኤክስፖርት አድራጊዎች በኢሌክትሮኒክ ሲንግል ዊንዶው ሲያመለክቱ ሚኒስቴሩ ለሲቪል አቪዬሽን ደብዳቤ በመጻፍ ማዕድኑ እንዲጓጓዝ እየተስተናገዱ ይገኛሉ።

ሆኖም ይህ አሠራር ከክልሎች ማዕድን በማሰባሰብ ለአዲስ አበባ ነጋዴዎች ሲያቀርቡ ለነበሩ ቀጥተኛ ኤክስፖርት አድራጊ ላልሆኑ አካላት ምቹ ያልሆነ ሁኔታ ፈጥሯል።

capital news

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...