መንግሥት ለዚህ ሁሉ አፈና፣ ስደትና ሞት የሚያሳየው ዝምታ

Date:

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በአርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ተደጋጋሚ ግድያ፣ አፈና እና መፈናቀል በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ።

ፓርቲው “መንግስት ጥቃቶቹን ለምን ማስቆም አልቻለም?፣አልፈለገም? እውነት ስለጥቃቶች ከህዝብ የተወሰረ ሌላ ጉዳይ አለ?” ሲል ጥያቄውን ያቀረበ ሲሆን የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ በዝምታ ሊያልፈው እንደማይገባ አሳስቧል።

ፓርቲው  ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው  መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጌቱ አሰፋ የተሰኙ አርሶ አደር በእርሻ ሥራ ላይ እያለ መገደላቸውን፣ ወደ 50 የሚጠጉ ዜጎች በታጣቂዎች መወሰዳቸውን እንዲሁም በሄላ ዘንባባ ቀበሌ  ዘውዴ ኃብቴ እና  አስራሱ ተስፋዬ መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል ብሏል።

በተጨማሪም በርካታ ዜጎች መታገታቸውን እና ቀሲስ ናርዶስ አሰፋ በጥቃቱ ቆስለው በሆስፒታል ሕክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። እንዲሁም ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ  ዘነበ ነጋሽ፣ ሳሙኤል ዋሌ እና ብሩህ አበራ የየተሰኙ ግለሰቦች መገደላቸውን አክሎ ገልጿል።

ኢሕአፓ መንግሥት ለዚህ ሁሉ አፈና፣ ስደትና ሞት የሚያሳየው ዝምታ ጥቃቱ “መዋቅራዊ ነው” እንድንል ያስገድደናል ያለ ሲሆን ጥቃቶቹን ማስቆም ባለመቻሉ ወይም ፍላጎት የሌለው በመሆኑ መንግሥት ለህዝቡ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል።

ፓርቲው አክሎም መንግስት በአርሲ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ አፈናዎች እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።

በተጨማሪም ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ ተጣርቶ ያለምንም ጉዳት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ፣ እስከዛሬ የተፈጸሙት ግድያዎች በዓለም አቀፍ ገለልተኛ አካል ተጣርቶ ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ መደረግ አለበት ብሏል።

ፓርቲው ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የጠየቀ ሲሆን ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጎ በደኅንነት ወደ ንብረታቸው እና ቀያቸው እንዲመለሱ ሁኔታዎች ይመቻቹ ሲል ጥሪ አቅርቧል።አክሎም የሁሉም ዜጎች እምነት ያለምንም ልዩነት የእኩልነት መብታቸው ሊከበር ይገባል።

ፓርቲው የዜጎች ሕይወት ከማንኛውም የፖለቲካ ጥቅም በላይ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት፣ ማንነትን እና ኃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በጽኑ ሊወገዙ እንደሚገባ አሳስቧል።

በእርግጥ በአርሲ የሚፈፀሙ ጥቃት የተደጋገመ እና ይህ የመጀመሪያውም ባይሆንም ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን የህዝብን አብሮ መኖር በማይፈለጉ የተፈፀመ ጥቃት ነው በሚል አውግዞ ነበር። ይሁን እንጂ በስፍራው የሚመለሱ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...