ተቋማት የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ሊኖራቸው ይገባል

Date:

የሳይበር ጥቃት በግለሰቦች መረጃ ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ፣ በተቋማት ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራና የስራ መስተጓጎል ሊያስከትል እንደሚችል ተገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃኑ በየነ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቋማት ለስራቸው አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ብቻ በጥንቃቄ ማሰባሰብና የግል መረጃን በአግባቡ መጠበቅ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ ብዙ ተቋማት ለስራቸው የማያስፈልጋቸውን መረጃ ጭምር የማሰባሰብ ልምድ እንዳላቸው አንስተው ለተለያዩ የሳይበር ጥቃቶች የሚጋለጡበትን ዕድል ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

መረጃ የሚያሰባስቡ ተቋማት መረጃው የት፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቀመጥና ማን ሊያገኘው እንደሚችል የሚያስቀምጥ ግልጽ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ሊኖራቸው እንደሚገባም አመልክተዋል።

በተጨማሪም የግል መረጃ የሚሰጡ ሰዎች መረጃቸው ለምን እንደሚሰበሰብና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የሳይበር ጥቃት በግለሰቦች መረጃ ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ፣ በተቋማት ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራና የስራ መስተጓጎል ሊያስከትል እንደሚችል ዶ/ር ብርሃኑ ጠቁመዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...