ሙዚቀኛ ብሌን ዮሴፍ #በመሰንበቻ

Date:

የሙዚቃ ዕውቀት + ጨዋነት ብሌኗ 🔥

” የቴዲ አፍሮን ያስተሰርያል አልበም እወደዋለሁ። “
<< የሙዚቃ ባለሙያ ብሌን ዮሴፍ >>

★ ክረምትን በጣም ነው የምወደው። ዳመና ሲሆን
የድሮ ትዝታዎችን ያመጣል። በተጨማሪ አዳዲስ
ነገሮች ለመጻፍ ፣ ዜማ ለመስራት ዝናብ ሲዘንብ
ይመጣልኛል።

★ የድምፃዊት ዶናት ተክሉ አልበም ላይ ፦
#ይቅርብኝ እና #አቅፎ_አድራሽ በተሰኙ
ሁለት ስራዎች ላይ ተሳትፊያለሁ።

★ ከዶናት ጋር በአጋጣሚ ነበር የተገናኘነው።
ዶናት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትዘፍን ስመለከታት
ኦ ማይ ጋድ ምን አይነት ድምፅ ነው ያላት
ብዬ ተደንቂያለሁ።

★ የዶናትን ይቅርብኝን ፅፌ ለኤልያስ ስልክለት
የተወሰኑ ግጥሞችን አውጥቷቸዋል።
መሐል ላይ ራሱ ግጥምና ዜማ ጨምሮ ነው
የሰራው።

★ አቅፎ አድራሽን ደግሞ ኤልያስ መልካ ጀምሮት
እኔ ነኝ ግጥሙን የጨረስኩት።

★ ግጥም ከሀይስኩል ጀምሮ በጣም እፅፍ ነበር።
ዜማ ሙዚቃ ከጀመርኩኝ በኋላ ነው መስራት
የጀመርኩት።

★ ግጥም ሰርቼ ማስቀመጥ እንጂ ለሰው ሰጥቼ
አላውቅም ነበር። አሁን ነው መስጠት የጀመርኩት።

★ የራሴን ሙዚቃ መስራት ሳስብ ክሬት የሆነችዋ
በዘፈኖቿ ውስጥ ትገለጻለች። እንደማንኛውም
ስራ የሚወድህም ፣ የሚጠላህም አይጠፋም
የሚል ስሜት ነው ያለኝ። ሁሉም የተሰጠው ልክ
አለው።

★ በፍቅር የምትሰራው ነገር ምንም ችግር የለውም።
የተገዛሁለትን ሀሳብ እፅፋለሁ።

★ ሙዚቃዬ ብዙ ሚሊዮን ቪው ቢታይ ደስ ይለኛል።
እንደሱም ስላልሆነ ደግሞ አልቆጭም።

★ ስለሀገሬ ፣ መንፈሳዊ ጥንካሬ ያለበትና እናትነት
የሚገዝፍበት ለመስራት ነበር አላማዬ።
የመጀመሪያ ስራዬ ያደረኩት ለዚህ ነው።

★ ሙዚቃ ለመማር ስሄድ ምንም አይነት የሙዚቃ
መሣሪያ ነክቼ አላውቅም ነበር።
ተመለከቱኝና ፍሉት ሰጡኝ።

★ ሳስተምር ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ፍሉት
እጫወታለሁ። ዜማ ሲመጣልኝ እሞክርበታለሁ።

★ ድምፃዊት ሚካያ በሀይሉን በአካል ሳላገኛቸው
ከቀሩ ሰዎች ውስጥ ናት። ነገር ግን
እንዳገኘኋት ነው የሚሰማኝ።

★ የሚካያ ስራዎቿን ስሰማው በጣም ነው ፊል
የማደርገው። በጣም ትልቅ ደራሲ ናት።
ዜማዎቿ እሷን ይመስላሉ።

★ ሚካያ ማንነት በሚባለው ነገር ራሷን ናት።
የሀሳብ ሰው ናት። ፍቅርን የምትገልፅበት
ነገር በጣም ይገርማል።

★ የሚካያን ስራ በፍሉት ከሰራሁ በኋላ
እናቷን አገኘሁ። አሁን ከሚካያ ቤተሰቦች ጋር
ቤተሰብ ሆነናል።

★ ከምግብ ጥሬ ስጋ እወዳለሁ ።

★ ለድሮ ሙዚቃዎች ልቤ ያደላል።

★ ተስፋ የሚያስቆርጥ ትችትም ሆነ አጉል ሙገሳ
ሁለቱም ይጎዳሉ።

★ ያለሙዚቃ መኖር አይቻልም።

★ አባቴ ንግድ ውስጥ ነበር። እኔ ግን
ነጋዴ መሆን አልችልም።

★ ራሴን በአንድ ቃል ስገልፀው ሳቂታና ሆደ ባሻ ነኝ።

★ በጣም የማደንቃቸውና የሚገርሙኝ ገጣሚያን ውስጥ
የሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ አክባሪና አድናቂ ነኝ።
ታላቅ ፀሐፊ ናቸው።

★ ሌላኛዋን ገጣሚ አለምፀሐይ ወዳጆን በጣም
እወዳታለሁ። አደንቃታለሁ። ስለ አለምፀሐይ
ከዚህ በላይ ሊነገርላት ይገባል። መከበር አለባት።

★ ወደዚህኛው ዘመን ስመጣ ደግሞ
ናትናኤል ግርማቸውን በጣም አደንቀዋለሁ።
በጣም ውብ የሆኑ ሀሳቦችና ቃላቶችን
ተጠቅሞ በጣም አቅልሎ ቆንጆ አድርጎ
ነው የሚገልፀው።

★ ከማደንቃቸው አልበሞች ውስጥ
የቴዲ ታደሰ #ዝምታ አልበም እንዳለ ሆኖ ፦
የእጅጋየሁ ሽባባው ( ጂጂ ) #አቤት_ውበት
አልበም ለእኔ የምንጊዜውም ምርጥ ስራ ነው።

★ የሚካያ በሀይሉ ሁለተኛ አልበም።

★ የቴዲ አፍሮ #ያስተሰርያል አልበምን በጣም
እወደዋለሁ።

★ አልበም ለመስራት እየሞከርኩኝ ነው።

የሙዚቃ ባለሙያዋ ብሌን ዮሴፍ
ከFm አዲስ 97.1 #መሰንበቻ የሬዲዮ ፕሮግራም
ላይ ከአዘጋጅና አቅራቢው ጋዜጠኛ ሰለሞን ጫላ
ጋር ያደረገችው አዝናኝ ቆይታ ይኽንን ይመስላል።

Solomon Challa እንደሁልጊዜውም በደንብ ተዘጋጅተህ
ስለምታቀርባቸው እንግዶች በቂ መረጃ ሰብስበህ
በጣፋጭ አንደበትህ በግሩም ሁኔታ በማቅረብ
ቅዳሜ ጠዋታችንን ስለምታሳምርልን 🙏

FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ 🙏

Blen Yosef ብሌኗ የሙዚቃን ዕውቀት ከጨዋነት
ጋር አጣምረሽ የያዝሽ ፣ ሙያሽን ለተተኪው ትውልድ
እያስተላለፍሽ ፣ እየቀረፅሽ ያለሽ የምትወደጂ
ባለሙያ ፈጣሪ ዕድሜና ጤና ይስጥሽ።

አክባሪሽና አድናቂሽ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት አባታቸው...

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል

ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ፤ አገራቸው...

ሱዳን ዉስጥ ለሦስት ዓመታት የተካሄደው ጦርነትን ሰለ ማቆም

የሱዳን ብሔራዊ ጦር ለሦስት ዓመታት የተካሔደውን ጦርነት ለማቆም አሜሪካ...