ሦስቱም ብፁዓን አባቶች ጥፋታቸውን አምነው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ይቅርታ ጠይቀዋል

Date:

የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የብፁዓን አባቶች አስተምሮን በተመለከተ ውሳኔ አሳለፈ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ የብፁዓን አባቶች አስተምሮ በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የሊቃውንት ጉባኤ በሦስት ብፁዓን አባቶች ማለትም ፦
– በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ
– በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሊቀ ጳጳስ
– ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ጳጳስ በተላለፉ ትምህርቶች ላይ ያቀረበውን የስህተት ትምህርት የሚያሳይ አስተያየትና የውሳኔ ሐሳብ መመልከቱን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ምልዓተ ጉባኤውም የሦስቱን አባቶች አስተያየት አዳምጦ ውሳኔ አሳልፏል።

ሦስቱም ብፁዓን አባቶች ጥፋታቸውን አምነው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ይቅርታ ጠይቀዋል።

በሊቃውንት ጉባኤ የቀረበው እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሚያምኑ እና የሚያስተምሩ መሆኑን በመግለጽም ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንደጠየቁ ተገልጿል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ይቅርታቸውን ተቀብሏል።

ያስተላለፉትን የስህተት ትምህርት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት / EOTCTV / ላይ ቀርበው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል አስተምህሯቸውን አርመውና አስተካክለው  እንዲያስተላልፉ መመሪያ ሰጥቷል።

ወደፊትም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራን  የሃይማኖት ትምህርት ሳይሸራረፍ ለትውልድ ለማስተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና በአከራካሪ ጉዳዮች በግለሰብ ደረጃ ምላሽ እንዳይሰጥ ጉባዔው ወስኗል።

መረጃ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው ያገኘው።

EOTC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...