ሩሲያ ከዩክሬን የተወነጨፉባትን 105 ድሮኖች መትታ መጣሏን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አስታወቀ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር 105 ድሮኖች የተተኮሱት ትላንት ሌሊት እንደሆነ የገለጸ ሲሆን ከ105 ድሮኖች መካከል 35 የሚሆኑት በሞስኮ ከተማ ያነጣጠሩ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ሁለቱ ሃገሮች የሚያደርጉት ድርድር ፍሬ ሊያፈራም ያልቻለ ሲሆን፤ ሩሲያም ትሁን ዩክሬን በድሮን እና የሚሳኤል ተኩስ አቁም ላይ እርስ በራሳቸው እየተወቃቀሱም መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡
ሮይተርስ ላይ እንደሰፈረው መረጃ የሩሲያ ሃይሎች በተለይም በፖክሮቭስክ ከፍተኛ መስፋፋት እያደረጉ ነው።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ በአንጻሩ የዩክሬን ወታደሮች በፖክሮቭስክ ብርቱ ውግያ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ እና የጀርመን መሪዎች ዩክሬንን መርዳት ላይ ያለመ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
