የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በሚደረገው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል ገለጹ።
ራያ አርሰናል ከኒውካስትል ጋር 2 ለ 2 አቻ በተለያየበት ጨዋታ በትከሻ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ወጥቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር በቻምፒዮንስ ሊግ 1 ለ 1 አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ አልተሰለፈም፤ ኬፓ አሪዛባላጋ በእሱ ምትክ ተሰልፎ ነበር።
አርቴታ ራያ ለሲቲው ጨዋታ ዝግጁ ሊሆን እንደሚችል ሲገልጹ፣ ከጨዋታው በፊት ያለውን ጊዜ ተጠቅመው ተጫዋቾችን ወደ ሙሉ የአካል ብቃት ሁኔታ ለማምጣት እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
አሰልጣኙ ሁሉም ተጫዋቾች ለቡድኑ ዝግጁ መሆንና በተሻለ የአካል ብቃት ሁኔታ ላይ መገኘት እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።
