በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የገቢዎች ቢሮ ሠራተኛ መስለው ነጋዴዎችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በሕዝብ ጥቆማ መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል ነጋዴዎችን በ100 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው በማስፈራራት፣ 50 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ይጠይቁ እንደነበር ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ስምና መታወቂያ ተጠቅመው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው ሲገለጽ፣ በእጃቸው የገቢዎች ቢሮ መታወቂያና የመሬት ባለሙያ የሚያሳይ ሌላ ሐሰተኛ መታወቂያም ተገኝቷል።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን፣ ነጋዴዎች የገቢዎች ቢሮ ሠራተኞችን መታወቂያ በመጠየቅና ባርኮዱን በስልክ በመቃኘት ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል
