ሰሞንኛ

Date:


(በእውቀቱ ስዩም)


ሰሙኝማ! በቀደም አነቃቂ ሀሳብ አቅራቢው ማንያዘዋል ምግብ ቤት ጎራ አልሁ፤ ያው እኔ ከተነቃቂዎች መሀል አይደለሁም፤ ግን ችግሩ ከኔ ሳይሆን አይቀርም፤ የሚያፈስ ጣራና የረጠበ ፍራሽ የሚያነቃኝ ሰው አይደለሁም፤ ምግቡ ግን በስምአብ ! ገራሚ ነው፤ ጣት ብቻ ሳይሆን ክርን አያስቆረጥማል! አጋነንህ በሉኝና ወደፊት ያገራችን ምግብ በሶስት የሚከፈል ይመስለኛል፥

የፍስክ ምግብ፥ የጦም ምግብና የማኔ ምግብ፤ ፎሰሴ የተባለው ምግብ በተለይ የሚዳሰስ ቅርስ ማለቴ ቁርስ ሆኖ መመዝገብ አለበት፤ ገና ከጉሮሮህ ሳይወርድ የሶስት ፈረስ ጉልበት ይሰማሀል፤ ብርድልብስ እንደ መሀረብ ማጠብ የሚያስችል አቅም ያጎናጽፍሀል ፤


እንዲያውም አንድ ጉዋደኛየ ባለፈው ፎሰሴ በልቶ መንገድ ሲያቋርጥ፥ ሲኖትራክ ገጨው፤ አሁን ሲኖትራኩ ጋራጅ ገብቶ እየተጠገነ ነው፤
የምር ይሄ ማስታወቂያ አይደለም ! የማኔን ቤት ጎብኙለት፤ እኛ ሙድ ስንይዝ እሱ ብርና ደንበኛ በመያዝ ላይ ነው::


ክረምቱ እየተገባደደ ነው
“ቡሄ እየመጣነው !
ያ ማበጠር የተነሳነው!”
እኔ ብዙ ጊዜ ረቂቅ ነገሮችን በምሰል ካላሰብሁዋቸው አይገቡኝም፤ ቡሄን ሳስብ፥ ሰይፉ ፋንታሁን የደብረብርሀን በርኖስ ለብሶ wireless ጭራ ሲነሰንስ ነው የሚታየኝ፤


በኛ ሰፈር ዱላ ይዞ ያልተሰማራ ፈላ የለም፤ ዘንድሮ ቡሄ ለየት የሚያደርገው ህጻናት ብቻ ሳይሆን አዋቂዎችም ፥ አይናቸውን በጨውና በበረኪና አጥበው መሳተፋቸው ነው፤


ቅድም አንድ ያምሳ አመት ጎልማሳ በህጻናቱ መሀል ተቀላቅሎ ጥሩንባ እየነፋ እኔ በር ላይ ሲጨፍር ነበር ፤ አምሳ ብር ሰጥቼ አርባ ብር መልስ ከተቀበልሁት በሁዋላ፥ “ ግን በቡሄ አዋቂዎች እንዲጨፍሩ ባህሉ ይፈቅዳል እንዴ?” ስል ጠይቅሁት፤


ሰውየውየ ምን ብሎ መለሰ?
“ባህሉ ባይፈቅድም የኑሮ ውድነቱ ይፈቅዳል”🙂

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...