ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ በሜዲካል ላቦራቶሪ፣ በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኒውትሪሽን እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 50 ተማሪዎች በ10ኛ ዙር መርሃ ግብር አስመርቋል።
ኮሌጁ የህክምና ትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በጤናው ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት በተለያዩ የትምህርትና የስልጠና መርሃ ግብሮች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል ።
ኮሌጁ በ2016 በዓለም አቀፉ የህክምና ትምህርት ተቋማት ዝርዝር (World Directory of Medical Schools) ውስጥ መካተቱን እንዲሁም የተማሪዎችን ተግባራዊ ብቃት ለማጠናከር ማዕከላትን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ኮሌጁ የህክምና ትምህርት ጥራትን የምርምር አቅምንና የሙያ ስልጠናን በማጠናከር እስከ 2030 ዓ.ም የሚዘልቅ የልማት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑ ጠቁሟል።
የዛሬው 10ኛ ዙር የተማሪዎች ምረቃ ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት የሚያሳይ እና ተመራቂዎቹም ያገኙትን እውቀትና ሙያዊ ክህሎት ለህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ማሻሻል እንዲያውሉ አደራውን ሰጥቷል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም የኮሌጁ አመራሮች፣ ተመራቂዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና የተለያዩ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
