ሳይንስ እንጂ ፖለቲካ ሕፃናትን አይታደግም

Date:

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በቅርቡ በአሜሪካ የክትባት ፖሊሲ ላይ የታዩ ለውጦች ከዓመታት ሳይንሳዊ ማስረጃዎች ጋር የማይጣጣሙ መሆናቸውን በመግለጽ ስጋቱን አጋለጠ።

ድርጅቱ ክትባቶች ህጻናትን ከገዳይ በሽታዎች ለመከላከል እጅግ አስተማማኝ መሣሪያዎች መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጧል።

የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ፣ የክትባት መርሃ-ግብሮች የሚቀረጹት ህጻናት ለበሽታ ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበትን ጊዜ፣ የክትባቶች የመከላከል አቅም የሚጠነክርበትን ወቅት እና የትኞቹ ክትባቶች በአንድ ላይ ቢሰጡ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን በሚያሳዩ ጥናቶች ላይ ተመስርቶ መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ የሚታዩ የፖሊሲ ለውጦች እነዚህን ሳይንሳዊ እውነታዎች ያላገናዘቡ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል።

እንደ ድርጅቱ መግለጫ፣ የኤም.ኤም.አር (MMR) ክትባትን ጨምሮ ማንኛውም ክትባት ኦቲዝምን (Autism) እንደማያስከትሉ ዓለም አቀፍ መረጃዎች በተደጋጋሚ አረጋግጠዋል።

ክትባቶችን መከልከል፣ ጊዜያቸውን ማዘግየት ወይም የመስጫ መርሃ-ግብራቸውን መለወጥ ለተጨማሪ ደህንነት የሚፈይደው ነገር እንደሌለ የገለጸው ድርጅቱ፤ ይልቁንም ህጻናትን መከላከያ ለሌላቸው ገዳይ በሽታዎች አጋልጦ እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አክሎም፣ የክትባት ፖሊሲዎች መወሰን ያለባቸው የየሀገሩን ነባራዊ ሁኔታ፣ የጤና ሥርዓት እና የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት ባደረጉ ገለልተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች እንጂ በፖለቲካዊ ተጽዕኖ መሆን እንደሌለበት አሳስቧል።

ማንኛውም የክትባት ውሳኔ በጥብቅ እና ግልጽ በሆነ ሳይንሳዊ ግምገማ ላይ ብቻ ሊመሰረት እንደሚገባም ድርጅቱ ጥሪውን አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...