ስምረት ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባዔውን አካኼደ

Date:

ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ዛሬ የመጀመሪያ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ከተማ አካሄደ።

ሰኔ 1/2017 ዓ.ም በተካሄደው ጉባዔ አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ የቀድሞ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እንዲሁም ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ተገኝተዋል።

በዛሬው ስብሰባ ክልላዊና አገራዊ አሁናዊ ሁኔታ ፣ የፓርቲው የምስረታ ሂደት ፣ የፓርቲው ረቂቅ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ማኒፌስቶ ላይ ወይይት ተደርጎበታል።

በተነሱት ሁሉም አጀዳዎች ላይ መግባባት እንደተደረሰም ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፓርቲው ውይይቱን ሲቋጭ የቀጣይ ትግል የትኩረት አቅጣጫዎች ያስቀመጠ ሲሆን በአጭር ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከሁሉም ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ፓርቲው እቅዶቹ ለማሳካት ወጣቶች ፣ ሙሁራንን ሴቶች ለማሳተፍ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ቀን በተካሄደው የስምረት ፓርቲ ጉባዔ በፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት የሆኑና ከትግራይ ውጪ የሚገኙ አባላቱ መሳተፋቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በስብሰባው የተሳተፉ የካቢኔ አባላት ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ የስቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊ እና ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃዲቕ የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...