ሹመት እየተሰጠው ያለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) !

Date:

ከሰሞኑ የካዛኪስታን የመንግስት ፈንድ በማዕከላዊ እስያ የመጀመሪያ ነው  የተባለለትን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ገለልተኛ የቦርድ ዳይሬክተር አስተዋውቋል።

ሥርዓቱ “SKAI” የሚባል ሲሆን እንደ ፋይናንስ እና አስተዳደር ያሉ የፈንዱ ተግባራት ውሳኔ ላይም ድምፅ መስጠት ይችላል።

ከ2008 ጀምሮ ባሉ የውስጥ ዶክመንቶች መሰልጠኑ ደግሞ ሚዛናዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ያደርገዋል ተብሏል።

ካዛኪስታን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራች የምትገኝ ሲሆን የሰው ሰራሽም አስተውህሎት ምርምር ላይ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ መመስረቷም ተገልጿል።

በተመሳሳይ ዜና ከዚህ በፊት አልባኒያ በዓለማችን የመጀመሪያውን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሆነች ሚኒስትር መሾሟ ይታወሳል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚኒስትር በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሾማበት ወቀትም ሙሉ ለሙሉ ከሙስና ነፃ መሆኑ ተገልፆ ነበር።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚኒስትሯ በፓርላማ ንግግር ባደረገችበት ወቅትም ” ሰዎችን ለመተካት ሳይሆን ለመርዳት ነው የመጣውት” ብላለች።

ዲዬላ የሚል ስያሜ የተሰጣት ይቺ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የለማች ሚኒስትር  የተሾመችው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሚኒስትር ተደረጋ ነው።

ፈጣን ለውጥን እያመጣ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አሁን አሁን በከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ ቦታዎች ላይም ጭምር እየገባ ሲሆን አንዳንዶች ነገሩን ከጥቅሙ ይልቅ በስጋትነት እያነሱት ይገኛሉ።

መረጃው የተገኘው ከዩሮ ኒውስ እና ከኤቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...