በኢትዮጵያ ከ8 ሴቶች ውስጥ አንዷ በጡት ካንሰር ትያዛለች

Date:

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ወደ 10,000 የሚደርሱ  ሰዎች በጡት ካንሰር ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሎ እንደሚገመት የጤና ሚኒስቴር፣ የጡት ካንሰር ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው የጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብር ላይ ተገለጸ፡፡

በመርሃ ግብሩ  በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ፣ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች መካከል ቀዳሚውን ደረጃ የሚይዘው የጡት ካንሰር ሲሆን፤ በየዓመቱ ወደ 16,000 የሚጠጉ ሴቶች በጡት ካንሰር ይያዛሉ ተብሎ ይገመታል።

  በተጨማሪም በየዓመቱ ወደ 10,000 ሰዎች በጡት ካንሰር ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሎ እንደሚገመት በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ 

በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሰር ታማሚዎች ወደ ህክምና የሚሄዱት ከፍተኛ ደረጃ ላይ  ከደረሰ በኋላ ሲሆን፤ ለዚህም ደግሞ ዋንኛው ምክንያት  በጡት ካንሰር ዙሪያ ያለው የግንዛቤ እጥረት ከፍተኛ በመሆኑ  ነው ተብሏል፡፡

በቀረበው ጥናት እንደተገለጸው፤ ከሦስት  የጡት ካንሰር ክስተቶች አንዱን  (እስከ 30% ክስተትን) በአኗኗር ዘይቤ ማስቀረት የሚቻል ሲሆን፤ ከ8 ሴቶች ውስጥ አንዷ በጡት ካንሰር ትያዛለች፡፡

ሴቶች በሚወልዱበት ጊዜ ጡት በደንብ ማጥባት፣ ሲጋራ አለማጨስና የአልኮል መጠጦችን አለመጠጣት፣ አካላዊ የክብደት መጠንን  ከልክ እንዳያልፍ መቆጣጠር ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር እንዲሁም በየትኛውም ጊዜ ከሚከሰት አደገኛ ጨረር  እራስን መጠበቅ እንደሚገባም በመርሀግብሩ  ተብራርቷል።

በተጨማሪም ሁሉም ሴቶች እራሳቸውን ከጡት ካንሰር ህመም ሊጠብቃቸው በሚችለው ቅድመ ልየታ ህክምና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የጡት ካንሰር ምርመራ በየጊዜው ሊያደርጉ ይገባልም ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...