ቀጠናዊ የኃይል ትስስር ለመፍጠር አዳዲስ የፋይናንስ ምንጮች እንደሚያስፈልጉ ተገለጸ

Date:

ቀጠናዊ የኃይል ትስስር ለመፍጠር አዳዲስ የፋይናንስ ምንጮች እንደሚያስፈልጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዎን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

አራተኛው “ምክንያታዊ የናይል ወንዝ አጠቃቀም እና ቀጣናዊ ውህደት አመታዊ ፎረም” በምህጻረ ቃሉ አፍሪ-ራን ቀጠናዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡

ኮንፈረንሱ “ቀጠናዊ የሀይል ትስስር ለአካታችና ዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻዎች አካላት በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) ኮንፈረንሱ በአካባቢው ትብብርን ለማጠናከር ጥሩ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።

በአፍሪካ ሚሊዮኖች ከመብራት አገልግሎት ውጪ ሆነው ኑሯቸውን እየገፉ እንደሚገኙ የገለጹት ሚኒስትሩ አክለውም “ቤቶቻችንን ለማብራት፣ ኢኮኖሚያችንን ለማጎልበት፣ እና ወጣቶቻችንን ለማነሳሳት የጋራ ፍላጎታችንን እናሰባስብ” ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቀጠናዊ የኃይል ትስስር አዳዲስ የፋይናንስ ምንጮችን እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ለዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም አስተማማኝ እና ፍትሃዊ የኃይል አቅርቦት መሰረት ሆኖ ማገልገል አለበት ያሉ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የጋራ መሰረተ ልማት፣ የተጣጣሙ ፖሊሲዎች እና ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ንግድ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳን እቅዶች ለማንሳት ወሳኝ መሆናቸውን አስረድተዋል።

አፍሪራን ፍትሐዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርህ የናይል ወንዝ ውሃ አጠቃቀም ገዢ መርህ በማድረግ በናይል ወንዝ ፍትሐዊነት ማረጋገጥ እንዲቻል አላማ ይዞ የተቋቋመ አመታዊ ቀጣናዊ ኮንፈረንስ ሲሆን በዚህ አመት በዋናነት ትኩረቱን የመንግሰትና የግል ሴክተር ትብብር የፋይናንስ ምንጮች ላይ በስፋት አድርጎ ተካሄዷል።

Addis standard

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...