በመዲናዋ ከተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ውጭ ሲሰሩ የተገኙ ከ550 በላይ ነጋዴዎች መታገዳቸው ተገለጸ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ ከተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ውጭ ሲሰሩ የነበሩ ከ550 በላይ ነጋዴዎች ከንግድ ዘርፍ ውጭ እንዲሆኑ እና በሕግ እንዲቀጡ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አሸናፊ ብርሀኑ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ በከተማዋ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ድንገተኛ እና የቤት ለቤት ክትትል በማድረግ እርምጃ ተወስዷዋል።

በተያዘው ዓመት 10 ወራት ውስጥ ከ400 ሺሕ በላይ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር መደረጉን የገለጹ ሲሆን፤ ድንገተኛና የቤት ለቤት ቁጥጥር ከተደረገባቸው ከእነዚህ ነጋዴዎች መካከል ከ20 ሺሕ በላይ በሚሆኑት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

“እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከልም 550 የሚሆኑት ከንግድ ዘርፉ እንዲገለሉና በሕግ እንዲጠየቁ ተደርገዋል” ብለዋል።

በተለይም ያለዘርፋቸው በሚነግዱ፣ ፈቃድ ሳያሳድሱ ማህበረሰቡን ከተቀመጠው መመሪያ ውጭ ላልተገባ ወጭ በሚዳርጉ ወይንም ከተቀመጠው ዋጋ ውጭ የሚሰሩ እና ተያያዥ የሆኑ ሕገ-ወጥ ንግዶችን በሚያከናውኑ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።

ከተቀመጠው መመሪያና ከዘርፋቸው ውጭ ሲሰሩ የተገኙ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ ከአስተዳደራዊ እርምጃ እስከ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መደረጉንም ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ቢሮው በመዲናዋ ከተሰጣቸው ዘርፍና ከተቀመጠው መመሪያ ውጭ እንዲሁም፤ ማህበረሰቡን በሚያጭበረብሩ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም “ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ለማድረግ ህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ መስጠት ይገባዋል” ብለዋል።

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...