በሥራና ክህሎት ባለሥልጣን የቢሊዮን ብር ከባድ የሙስና ክስ

Date:

በሥራና ክህሎት  ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አለቃን ጨምሮ በ13 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ከባድ ሙስና ወንጀል ችሎት 16 ተደራራቢ ክሶች ቀረቡ።

ተከሳሾቹ የሚኒስቴሩ ሠራተኞች፣ የሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ፣ የአቶ ብርሃኑ አለቃ ባለቤት እና ሌሎች ግለሰቦች ናቸው።ዋና ተከሳሽ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አለቃ ሥራ አስኪያጅ እያሉ ፥ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (ELMIS) ላይ ወደ ውጭ ሀገራት ለሥራ የሚጓዙና የሙያ ብቃት ምዘና ሊጸድቅላቸው (COC Online) የሚገቡ ዜጎችን ያለ ምንም ወይም ያለ በቂ ሥልጠና የተለያየ መጠን ያላቸውን ገንዘቦችን በማስከፈል የሙያ ብቃት ምዘና እንዲጸድቅላቸው አድርገዋል።
ከፍተኛ የሆነ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘትም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለማይታወቁ (ሠራተኛ ላልሆኑ) ግለሰቦች በሲስተሙ ላይ የሙያ ምዘና (COC) የማጽደቅና የሙያ ምዘና ልዩ የአስተዳዳሪ (COC Special Admin) ሥልጣን እንዲኖራቸው አድርገዋል።

ከዚህ ወንጀል ድርጊት ወደ ውጭ ሀገራት ከሚሄዱ ዜጎች የሚሰበሰቡ ገንዘቦችን ለመቀበል ዓላማ በሐሰተኛ መታወቂያ ስማቸውን እንዲቀይሩ በማስደረግ እና የሌሎች ሰዎችን ፎቶ በመጠቀም በተለያዩ ባንኮች የባንክ ሂሳብ አስከፍተዋል።

በዚህም 1,134,609,241.93 (አንድ ቢሊየን አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) መጠን ያለው ገንዘብ በእነዚህ በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች እንዲገባ ማድረጋቸው በክሱ ላይ ሰፍሯል።

ከእነዚህ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ክፍያ በመፈፀም በራሳቸው እና ተከሳሽ በሆነች ባለቤታቸው ስም በአዲስ አበባ ውስጥ ፦

👉 6 መኖሪያ ቤቶች በ223,654,950 ብር፣

👉 በ68,144,738.03 ብር አንድ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ገዝተዋል።

በዚህም ተከሳሽ ብርሃኑ አለቃ በዋና ወንጀል አድራጊነት ለጊዜው ካልተያዘው ተከሳሽ ታምርአየሁ ጌትነት ጋር በመሆን በፈጸሙት ሥልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ብርሃኑ አለቃ ላይ ፦
• በወንጀል የተገኘን ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል፣
• ከባድ እምነት ማጉደል፣
• ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት ወንጀልን ጨምሮ በአጠቃላይ 4 ተደራራቢ ክስ ነው የቀረበባቸው።

በሌላ በኩል፣ ተከሳሽ ኤርሚያስ ተክሉ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሰራተኛ ስምሪት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በነበሩበት ወቅት ወደ ጆርዳን ሀገር 64,091 ዜጎችን በሀሰተኛ የቪዛ ሰነዶች ከሀገር እንዲወጡ በማስደረግ ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

አጠቃላይ በዚህ ምርመራ መዝገብ 13 ሰዎች ላይ እንደየተሳትፏቸው በጉቦ መቀበል፣ በሥልጣን መነገድ እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀሎች 16 ክሶች ቀርቦባቸዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...