በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ለመከላከል ጥሪቀረበ

Date:

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የ2019 ዓ.ም. የ16ቱ ቀናት የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ዘመቻን በይፋ ጀምሯል። ዘመቻው በሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል፣ የተጎጂዎችን መብት ለማስጠበቅና የተቋማት ተጠያቂነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

«ለተጎጂዎች ፍትሕ፤ ለወንጀለኞች ተጠያቂነት፤ ለሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ደህንነት» በሚል ሀገር አቀፍ መሪ ቃል የተጀመረው ዘመቻ፣ ከኅዳር 16 እስከ ታኅሣሥ 1 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚቆይ ሲሆን፣ «ትሰማ» በሚል መሪ ቃል የሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ደህንነት ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን፣ ዘመቻው የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ፣ የተቋማት ተጠያቂነት እንዲጠናከርና ጥቃትን መከላከል የሁሉም የጋራ ኃላፊነት እንዲሆን ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ሴቶች ለአካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲጂታል ጥቃቶች፣ ለልጅነት ጋብቻና ለሴት ልጆች ግርዛት ተጋላጭ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በፍርሃት፣ በማኅበራዊ መገለልና በቂ የድጋፍ አገልግሎቶች ባለመኖር፣ ብዙ ጥቃቶች ሪፖርት ሳይደረጉ እንደሚቀሩና ተጎጂዎች ፍትሕ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተገልጿል።

            የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ፌቨን አርአያ፣ ሴት ተኮር ግድያን በይፋ የሚያሳይ የዲጂታል መረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋና ጥቃቶቹን በሕግ ለይቶ የሚቀጣ ማሻሻያ እንዲታሰብ ጥሪ አቅርበዋል።

የጥቃት ጉዳዮችን በተገቢው ሁኔታ ለመመዝገብ፣ ለመከታተልና የተጎጂዎች ፍትሕ እንዲረጋገጥ የተቋማት ተጠያቂነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑም ተጠቁሟል።

         ለጥቃት ተጎጂዎች የመጠለያ፣ የሕግ ድጋፍ፣ የሕክምናና የሥነ ልቦና አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል ተቀናጅተው እንዲሰጡና አገልግሎቶቹ እንዲስፋፉ በቂ በጀት እንዲመደብ ጥሪ ቀርቧል።

የጥበቃ ማዘዣዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲተገበሩ፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የጥቃት ሪፖርቶችን በፍጥነት ተቀብለው ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ አስፈላጊነቱ ተገልጿል።

               መገናኛ ብዙኃን የተጎጂዎችን ክብርና ግላዊነት ጠብቀው በኃላፊነት እንዲዘግቡ፣ የትምህርትና የሥራ ተቋማት ከጥቃት ነጻ የሆኑ አካባቢዎች እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

የሃይማኖትና የማኅበረሰብ መሪዎች፣ ወንዶች፣ የልማት አጋሮችና መላው ማኅበረሰብ ጥቃትን በማውገዝ፣ ለተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግና የመከላከል ጥረቶችን በማጠናከር ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቀዋል።

          ሴቶችና ሴት ልጆች በደህንነት፣ በክብርና በእኩልነት የመኖር መብት ያላቸው መሆኑን በማስገንዘብ፣ ጾታዊ ጥቃትን መከላከል የመንግሥት፣ የሲቪል ማኅበረሰብና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑ ተጠቁሟል።

ዘመቻው የሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ድምጽ እንዲሰማ፣ ለተጎጂዎች ፍትሕ እንዲረጋገጥ፣ የጥቃት ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑና ሴቶች ከጥቃት ነጻ በሆነ ማኅበረሰብ እንዲኖሩ የጋራ ጥረት እንዲጠናከር ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፊፋ በሳይበር ጥቃት የመረጃ ስርቆት ደረሰበት

የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል የሆነው ፊፋ (FIFA) በሳይበር...

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ታወቀ

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ምርጥ ተጫዋች ተለይቶ...

ጠ/ሚ ዐቢይ፡ “መንግስት መቼ ይወድቃል?” ለሚሉ ግምቶች መሠረተ ቢስ ናቸው

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ይወድቃል በሚል የሚናፈሱ ግምቶች መሠረተ ቢስ...

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዳኛው በአወዛጋቢ ውሳኔዎች ከሜዳ ተሰናበተ

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ 2 ውድድር ላይ የተካሄደ ጨዋታን ይመራ...