የአንጋፋው ደራሲ Beljig Ali ቤልጅግ አሊ(ጌዲዮን ተስፋየ) የፃፈው አዲስ መፅሐፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ገበያ ላይ ይውላል። “በእኔ ስም አይሆንም” ቤልጅግ አሊ ቀለበቴን ስጧት እና ዕንባና ኩነኔ በተሰኙት ተወዳጅ መፅሐፎቹ ይታወቃል።
በዚህ መፅሐፉ ከሰፊ የህይወትና የንባብ ባህሩ የጨለፋቸው ውብና አጫጭር ታሪኮች በውብ አፃፃፍ ተሰድረው ቀርበዋል። ፈገግ ብለን ሳንጨርስ እያስፈገገን “ድሮ ቀረ” ልንል ስንል እየመለሰን ከምናብ እስከህያው ቀናችን ያመላልሰናል።
እንቢ ሊባል የሚገባውን እንቢ ማለት የማሸነፍና ያለማሸነፍ ጉዳይ ብቻ አይደለም ፤ የህሊና ፍትህን አለማዛባት ነው፣ ሰው በአገሩ ስም፣ በእምነትና በብሔሩ፣ በፆታና የፖለቲካ አቋሙ ግፍ ሲፈፀም “በእኔ ስም ምን ሲደረግ” ማለት መቻል አጃኢብ ነው።
በስማችሁ ምን እየተደረገ ነው? ነገ አብራችሁ በክፉ በደጉ ትከሰሱም ትመሠገኑም እንደሆን አይታወቅምና ስማችሁን ለማን እንዳዋሳችሁ በማን እንደተዘረፋችሁ አስተውሉ!! ቢያንስ ታሪክ “የሉበትም ነበር” የሚል ህያው ምስክር ይሆናችኋል!! ይነበብ
አሌክስ አብርሃ