በባህሬን ላይ በተፈጸመው ጥቃት ኢራን በአረብ ሀገራት ውግዘት ገጠማት

Date:

ኢራን በባህሬን የኢንዱስትሪ ተቋም ላይ በፈጸመችው ጥቃት የባህረ ሰላጤው ትብብር ምክር ቤት (GCC) እና የአረብ ሊግ ድርጊቱን አውግዘዋል። ጥቃቱ በተቋሙ ላይ የእሳት ቃጠሎና የንብረት ውድመት ያደረሰ ቢሆንም፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የባህሬን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት ኤምሬቶች ጥቃቱን በጽኑ በማውገዝ ከባህሬን ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። ሳዑዲ አረቢያ ኢራን የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጓና ዓለም አቀፍ ሕጎችን መጣሷን አውግዛለች፤ ኤምሬቶች በበኩላቸው ጥቃቱ የባህሬንን ሉዓላዊነት የጣሰ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል።

የመን፣ ሶሪያና ኩዌትን ጨምሮ በርካታ የአረብ ሀገራትም የኢራንን ድርጊት አውግዘዋል። ኢራን በበኩሏ የአሜሪካ የጦር ማዘዣ ማዕከላት ያሉባቸውን ጎረቤት ሀገራት ማጥቃቷን እንደማትተው እየዛተች መሆኗን ዘገባው አመልክቷል።

ዘገባው ከኳታር ኒውስ ኤጀንሲ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...