የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026 በተካሄደው የአረቢያን ካርጎ ሽልማት ላይ ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ ተብሎ ተሸልሟል።
አየር መንገዱ ይህንን እውቅና ያገኘው በአፍሪካም ሆነ በዓለም የፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ የካርጎ ማጓጓዣ አገልግሎት በመስጠት ያሳየውን አፈጻጸም ተመስርቶ ነው።
ለተከታታይ አራት ዓመታት የተገኘው ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ካርጎ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽንና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ያለውን ተወዳዳሪነትና አስተማማኝነት የሚያሳይ መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
