ከዚህ በፊትም እነዚህ ቤቶች ከከተማው አንዲጠፋ መመሪያ ተሰጥቶ ነበር፤ ግን አሁንም ድረስ ቤቶቹ መኖራቸውና በስራ ላይ መሆናቸው ታውቋል ተብሏል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥም የአዲስ አበባ ከተማ ከ #ቢንጎ ማጫወቻ እና የ #አረቄ መሸጫ ቤት ነፃ እንዲሆን ይደረጋል መባሉን ሰምተናል፡፡
ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ነው፡፡
ቤቶቹ እንዳይኖሩ ይደረጋል ያለው ተቋሙ ምክንያቴም ቤቶቹ የወንጀል ምክንያት በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡
የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቢንጎ ማጫወቻ እና በየመንደሩ ያሉ አረቄ ቤቶች የከተማው ወንጀል መፈልፈያ ቦታዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ይህንን ማስፈፀም ያልቻሉ ሀላፊዎችም በቦታቸው አይቀጥሉም ብለዋል፡፡
ሸገር 102.1
