የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ለ90 ደቂቃ ከተወያዩ በኋላ የሦስትዮሽ “የጋራ የሰላም መግለጫ” አውጥተዋል።የጋራ መግለጫው “የኒውክሌር ጦርነትን ማሸነፍ አይቻልም፤ መቼም ቢሆን ውጊያው መካሄድ የለበትም” ይላል።
አገራቱ የተጣራ የነዳጅ ምርት መጠንን ለመጨመርም ቃል ገብተዋል።
ውይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ፑቲን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጻ፤ ኪቭ እና አውሮፓ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ አይደሉም ብለዋል።
ትራምፕ ከፑቲን እንዲሁም ከዢ ጋር በተናጠል ውይይቶች አድርገዋል። የሩሲያውን ፕሬዝዳንት “ጓደኛዬ” ሲሉም ጠርተዋል።
ከዢ ጋር ከተወያዩ በኋላ አሜሪካ እና ቻይና የዩክሬንን ጦርነት ማስቆም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
የቻይና ብሔራዊ ጣቢያ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዢ ውይይቱን “አወንታዊ፣ ገንቢ እና እጅግ ውጤታማ” ሲሉ ገልጸውታል።
