በኢትዮጵያ “አዲስ የገበያ ማዕከል ይዘን መጥተናል” ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ

Date:

በኢትዮጵያ “ግብይትን ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መዝናኛ ጋር ያጣመረ ግዙፍና ዘመናዊ ሞል” በካቮድ ሪል እስቴት እየተገነባ መሆኑን ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ (LUXADDIS PROPERTIES) የተሠኘ ድርጅት አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሐመድ ሰዒድ፤ ዛሬ ጁመዐ ነሐሴ 2/2017 በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መግለጫ ላይ የአፍሪካ መዲና እና የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ፤ “ስጦታ ሞል” የተሠኘ ፕሮጀክት በከተማዋ እምብርት ላይ የመገንባት ሥራው እንደተጀመረ ይፋ አድርገዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ባለቤት ካቮድ ኮሜርሺያል እና በስጦታ ሞል ብቸኛ የሽያጭ ወኪል ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ በጋራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “ስጦታ ሞል የተለያዩ የስጦታ ግብዓቶችና ተዛማጅ አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ሥር በተመቻቸ ሁኔታ የሚሰበሰቡበት መሆኑን እንዲሁም የከተማችን አዲስ መልክና የግብይት ባህልን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር” የላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሙሐመድ ፈረጅ አስረድተዋል፡፡

ላክስ አዲስ ይዞት የመጣው ስጦታ ሞል፤ ከአራት ኪሎ፣ ከፒያሳ፣ ስድስት ኪሎ፣ ከመነንና ከሰሜን ሆቴል በእኩል ርቀት ላይ በሰው ሠራሽ ሐይቅ፣ በሰፊ መናፈሻ እና በአቅሷ መስጂድ የተከበበ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ከዘመናዊ የሱቆች በተጨማሪ ግብይትና መዝናኛን ያጣመረ አገልግሎት ስለሚሰጥ በደንበኞች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

18 ሺሕ ካሬ ሜትር አጠቃላይ ሥፋት የያዘውና በ18 ወራት ግንባታው እንደሚጠናቀቅ በተነገረው በስጦታ ሞል፤ የንግድ ቦታዎችን 50 በመቶ የሚደርስ ከወለድ ነፃ ብድር እንደተመቻቸ በላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ የሥራ ኃላፊዎች ተገልጿል።

በዛሬው እለት ከተሰጠው መግለጫ በኋላ በፕሮጀክቱ ባለቤት ካቮድ ኮሜርሺያል እና በስጦታ ሞል ብቸኛ የሽያጭ ወኪል ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ ኃላፊዎች የብቸኛ ሽያጭ ወኪልነት የፊርማ ሥነ ሥርዐት አካሔደዋል፡፡

የፊርማ ሥነ ሥርዐቱ የተካሄደው በላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሐመድ ሰዒድ እና በካቮድ ኮሜርሻል ቺፍ ኦፊሰር አቶ ፍሬው ታምሩ አማካኝነት ነው፡፡

በተጨማሪም

የሃገር ልጆች ድንቅ የእጅ ሥራ ውጤቶች በአንድ ስፍራ የሚከትሙበት ነው የተባለው ስጦታ ሞል፤ ዘላቂና አዋጭ ኢንቨስትመንት ለሚፈልጉ ሁሉ የተለየ ዕድልን ይዞ እንደመጣ የተገለጸ ሲሆን፤ የሱቅ ቦታዎችን በካሬ ከብር 240,000 ጀምሮ መግዛት እንደሚቻልና 50% የሚደርስ ከወለድ ነፃ ብድር እንደተመቻቸ በላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ የሥራ ኃላፊዎች ተገልጿል።

(ሚንበር ቲቪ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...