በደሌ ቢራ ፋብሪካ የተለያዮ ኃላፊነቶችን ለመወጣት በበደሌ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

Date:

በሃይንከን ኢትዮጵያ ስር የሚገኘውና ከተመሰረተ 37 ዓመታት ያስቆጠረው በደሌ ቢራ ፋብሪካ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በበደሌ ከተማ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

ሃይንከን ኢትዮጵያ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኀብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ በጠቅላላው በ 7 ሚልየን ብር ወጪ 22 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የወተት ላሞች እርባታ እና የዶሮ እርባታ ማዕከላት ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

በደራሽ የጋራ መኖርያ ቤት ፕሮጀክት አማካይነት 30 ቤቶችን ከእነ የጋራ መጸዳጃና ማብሰያ ቤቶች በ32 ሚልየን ብር ወጪ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። ሃይንከን ስምምነቱን የፈፀመው ከበደሌ ከተማ አስተዳደር ጋር ነው።

በተጨማሪም ሃይንከን ኢትዮጵያ በበደሌ ከተማ ለሚገኙ ሰንደይ ፋሚሊ የጤና ስፖርት ቡድን ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል።

የሃይንከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ባርት ዲ ክኒንክ በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኩባንያው ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ ሰፋፊ ሥራዎችን በመላ ሀገሪቱ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል። በተጨማሪም ሃይንከን ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ 14 ቢልየን ብር የግብር ግዴታውን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመወጣት ለኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጉን አስታውሰው ይኸም ከግሉ ዘርፍ በግብር ከፋይነት አንደኛ እንዳደረገው ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በበደሌ ቢራ አማካይነት ለበደሌ ከተማ አስተዳደር በግብር መልክ 172 ሚልየን ብር አስተዋፅኦ ማድረጉ ተጠቅሷል።

የሃይንከን ኢትዮጵያ የሰስቴይኔቢሊቲ የውጭ እና መንግስታዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ
በበኩላቸው ሃይንከን ኢትዮጵያ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣው የትግበራ አካላትን በማሳተፍ እንደሆነ ገልጸው፤ ለጅማ ዪኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላትና ምሁራን፣ ለበደሌ ከተማ አስተዳደር፣ ለሃይንከን ቤተሰቦች ምሥጋና አቅርበዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የሃይንከን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት፣ የበደሌ ፋብሪካ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ምሁራን፣ የበደሌ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ተሾመና ሌሎች አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የበደሌ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ድሬቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...