በጊኒ ቢሳው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተፈጸመ

Date:

በጊኒ ቢሳው የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመፈፀም የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮን አስረዋል።

ወታደራዊ አመራሮቹ በሃገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያም ቀርበው እሁድ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማገዳቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪ ሁሉንም የጊኒ ቢሳው ድንበሮች የዘጉ ሲሆን የሰዓት እላፊም አስቀምጠዋል።

ጊኒ ቢሳው ባለፈው እሁድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን ያካሄደች ሲሆን ውጤቱ በዛሬው እለት ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።

ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ የፕሬዚዳንቱ የምርጫ ተፎካካሪ የነበሩት ዲያዝ እና ለእርሳቸው ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩት የቀድሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ፔሬራም ታስረዋል።

ወታደሮቹ የጦሩን አዛዥ ጀነራል ና ንታንና ምክትላቸውን ጀነራል ቱሬንም ማሰራቸው ተሰምቷል።

ጊኒ ቢሳው ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣች በኋላ ባለፉት 50 አመታት 9 የመፈንቅለ መንግስት ተግባራትንና ሙከራዎችን አስተናግዳለች።

የ2 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያዋ ሃገር ሰፊ የባህር ዳርቻ ሲኖራት ለአደንዛዥ እፅ ዝውውር የተመቸች ስትሆን ተመድም “narco-state” የሚለውን ስያሜ ሰጥቷታል።

መፈንቅለ መንግስት ፈፃሚዎቹም መፈንቅለ መንግስቱን የፈፀሙት በእፅ አዘዋዋሪዎች የሚደገፉ ፖለቲከኞችን ሴራ ለመቀልበስ እንደሆነ ገልፀዋል።

BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...