በ7ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተጠናቀቁ

Date:

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር በተመሳሳይ 1-1 ውጤት አቻ ተለያዩ።

ቢኒያም ጌታቸው ለሀድያ ሆሳዕና ግብ ሲያስቆጥር፣ አስቻለው ታመነ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ የአቻነት ግብ አስቆጥሯል። በሌላው ጨዋታ ሳሙኤል ሳሊሶ ለኢትዮጵያ መድን ግብ ሲያስቆጥር፣ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ለፋሲል ከነማ አቻነት አስገኝቷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ11 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ፣ ሀድያ ሆሳዕና በ5 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮጵያ መድን በ8 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ፣ ፋሲል ከነማ በ4 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፋሲል ከነማ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ድል ማድረግ አልቻለም።

በቀጣይ መርሐግብር አርብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ድቻ ሲገናኝ፣ ቅዳሜ ኢትዮጵያ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና እና ወልዋሎ ዓ.ዩ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ። እሁድ ደግሞ ፋሲል ከነማ ከመቻል ጋር ይገናኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መቻል አትሌቲክስ ክለብ ሶስት ዋንጫዎችን አሸነፈ

6ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በአዲስ...

በሰሜን ጎንደር በየወሩ ከ30 በላይ አዳዲስ የኤችአይቪ ተያዦች እየተመዘገቡ ነው

በሰሜን ጎንደር ዞን በየወሩ ከ30 በላይ አዳዲስ የኤችአይቪ ተያዦች...

የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርና ዋናው ስፖርት አጋር ሆኑ።

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርና ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት...

12 ሀገራት የሚሳተፉበት የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግር ኳስ ሻምፒዮና...