ቦርዱ አከራካሪ የሆኑ ምርጫ ክልሎችን በተመለከተ የተላለፈውን ውሣኔ ይፋ አደረገ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፌዴሬሽን ም/ቤት በአማራ እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥታት አከራካሪ የሆኑ ምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሣኔ ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ላይ በተመለከተው መሠረት ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ እየተዘጋጀባቸው ያሉትን ምርጫ ክልሎችና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ይህንኑ ቦርዱ ያወጣውን የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች ዝርዝር ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ለቦርዱ በጻፈው ደብዳቤ በትግራይ እና በአማራ ክልላዊ መንግሥታት መካከል አከራካሪ ሆነው የቆዩት የአምስት ምርጫ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ የሁመራ፣ የአዲረመፅ፣ የኮረም አፍላ፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ምርጫ እንዲደረግ ምክር ቤቱ መወሠኑን ለቦርዱ አሳውቋል ብሏል፡፡

የክልል ምክር ቤት ምርጫው በአካባቢዎቹ ላይ የተነሣው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ መንግሥት ውሣኔ ሲፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ መወሠኑንም ምክር ቤቱ ማሳወቁን አብራርቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...