አንጋፋውና ተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ በሰሜን አሜሪካ በምሳሌ ግብረሰናይ ድርጅት በተከናወነው ‘ምሳሌ አዋርድ ‘ የ2025 የዘመን ተሻጋሪ ዘርፍ የዓመቱ ተሸላሚ ሆነ።
በዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተው ተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ፥ በአትላንታ በድምቀት በተከናውነው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ “ማንበብና መፃፍ” እና ከድምፃዊ ንዋይ ደበበ ጋር የተጫወተውን “ከእሷ ጋር እያለሁ” የተሰኙ ሁለት ሙዚቃዎችን ተጫውቷል።
ፀሐዬ ዮሐንስ ካበረከታቸው የሙዚቃ አልበሞች መካከል ተይ ሙኒት፣ ፍንጭቷ፣ ሳብሳም፣ ጡር ነው፣ ተባለ እንዴ፣ ሳቂልኝ የተሰኙት ተጠቃሽ ናቸው።
ተመስገን ኡካሬ
