- ዘለንስኪ የሚገኙበት ዕድል ይኖራል ተብሏል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፊታችን አርብ በአላስካ ተገናኝተው ስለ ዩክሬን ጦርነት እንደሚወያዩ ተገለጸ።
አላስካ ለሩሲያ ቅርብ ስለሆነች ምቹ ቦታ እንደሆነም ተገልጿል። በዩክሬን በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
ዩክሬን ጦርነቱን ለመግታት ግዛቶች መስጠት ይኖርባታል የሚል ሐሳብ ከትራምፕ ከተደመጠ በኋላ ነው ስለ ውይይቱ የተሰማው።
“በሦስት ዓመት ተኩል ውስጥ ለዚህ ግዛት ብዙ ሩሲያውያንና ዩክሬናውያን ሞተዋል። ውስብስብ ጉዳይ ነው። የተወሰኑትን እናስመልሳለን። የምንለዋወጣቸው ግዛቶችም ይኖራሉ። ለሁለቱም ወገን የሚበጀው ይሄ ነው” ብለዋል ትራምፕ።
የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት ባገኘው መረጃ መሠረት፤ ሩሲያ አጠቃላይ ዶንባስን የምትወስድበትና ክሬምያን ይዛ የምትቀጥልበት የሰላም ስምምነትን የአውሮፓ መሪዎች እንዲቀበሉ የማድረግ ዕቅድን አሜሪካ ይዛለች።
ሩሲያ በከፊል የያዘቻቸውን ኬርሶን እና ዛፖሪዚያ ግዛቶችን የምትመልስም ይሆናል።
አንድ ከፍተኛ የዋይት ሀውስ አመራር ለሲቢኤስ እንዳሉት፣ በቀጣይ አርብ በፑቲንና ትራምፕ መካከል የሚካሄደው ውይይት ላይ ዘለንስኪ ሊገኙ የሚችሉበት ዕድል ይኖራል።
(BBC)
