ትራምፕን ያበሳጨው ውሳኔ

Date:


የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በካናዳ ላይ የትራምፕ አስተዳደር የጣለውን ታሪፍ “ለመቀልበስ “ድምፅ ሰጠ።

የታችኛው ምክር ቤት (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣የህግ መምሪያው) ድምፅ መስጠቱና የራሱን ውሳኔ ማሳለፉ ምልክታዊ ተደርጎ ተወስዷል።

219 ለ211 በሆነ ድምፅ ትራምፕ በካናዳ ላይ የጣሉትን ታሪፍ እንዲያነሱ ውሳኔ ቢተላለፍም ብዙ ሂደቶች ይቀራሉ።

ሰድስት ሪፐብሊካኖች ዴሞክራቶቹን ተቀላቅለው ድምፃቸውን ሰተዋል።

ውሳኔው እንዲፀድቅ የአሜሪካ ሴኔት (የላይኛው ምክር ቤት፣የህግ መወሰኛ ምክር ቤት) ማፅደቅ ይኖርበታል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም ውሳኔውን ተከትለው ህግ አድርገው ሰነዱ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል።

ለዚህም ነው ውሳኔው ምልክታዊ እንጂ የመፅደቁ ነገር ጊዜ የሚወስድ ነው የሚባለው።

ትራምፕ ካናዳ በቅርቡ ከቻይና ጋር ያቀደችውን የንግድ ስምምነት ተከትሎ መቶ በመቶ ከካናዳ በሚገቡ ምርቶች ላይ ታሪፍ እጥላለሁ በሚልም ዝተዋል።

ድምፅ እየተሰጠ ባለበት ሰዓት ፕሬዚዳንቱ በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ላይ ዴሞክራቶቹን ደግፎ የሚቆም ሪፐብሊካን በምርጫ ወቅት ዋጋ ይከፍላል ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ፅፈው ነበር ።

ውሳኔው በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ የሀሳብ ልዩነቱ እያየለ መምጣቱነወ የሚጠቁም ነውም ተብሏል።

የአልጀዚራ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...