ትራምፕ የቻይናው መሪ ከፑቲን እና ከኪም ጋር በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው አሉ

Date:

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ከሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች ጋር በጥምረት በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ወቀሱ።

ትራምፕ ይህንን ያሉት ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ታላቅ ወታደራዊ ትዕይንት ረቡዕ፣ ነሐሴ 28/ 2017 ዓ.ም ማካሄዷን ተከትሎ ነው።

በዚህ ታላቅ የወታደራዊ በዓል የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ 26 መሪዎች ተገኝተዋል።

ትራምፕ ለፕሬዚዳንት ሺ “በአሜሪካ ላይ በጋራ እያሴራችሁ ላላችሁት ለቭላድሚር ፑቲን እና ለኪም ጆንግ ኡን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርብልኝ” ሲሉ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘ ማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ትራምፕ ከዚህ ቀደም በቻይና፣ ሩሲያ እና ሌሎች አገራት መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአሜሪካ ተግዳሮት ጋርጧል መባሉን አጣጥለው ነበር።

ትራምፕ በዚሁ የማህበራዊ ገጽ ልጥፋቸው ላይ አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለቻይና የሰጠችውን ከፍተኛ “መስዋዕትነት” አውስተዋል።

“በርካታ አሜሪካውያን ለቻይና ድል እና ክብር ሲሉ ሞተዋል። ለጀግንነታቸው እና መስዋዕትነታቸው በትክክል እንደተከበሩ እና እንደሚታወሱ ተስፋ አድርጋለሁ” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...