የ2024/25 ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ቶተንሀም ማንችስተር ዩናይትድን 1ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ።
የቶተንሀምን ወሳኝ የማሸነፊያ ግብ ብሬናን ጆንሰን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ቶተንሀም በታሪኩ ሶስተኛውን የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።
አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ክለብ በተረከቡ ሁለተኛ አመታቸው ዋንጫ የማሸነፍ ሪከርዳቸውን አስቀጥለዋል።
ቶትንሀም በዚህ ሲዝን ማን ዩናይትድን አራት ጊዜ አሸንፏል በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን ይሄንን ያክል ጊዜ የተሸነፈው ኤቨርተን ነበር በ1985-86።
ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአውሮፓ መድረክ የማይሳተፍ ይሆናል።
