ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት የምታስገባቸውን ምርቶች ከቀረጥ ሙሉ በሙሉ ነጻ ልታደርግ ነው

Date:

ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት የምታስገባቸውን ምርቶች ከቀረጥ ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በቻይና-አፍሪካ ስብሳባ ላይ አስታውቃለች።

ከዚህ ቀደም የቻይና የቀረጥ ነጻ እድል ተጠቃሚ የነበሩት 33 የአፍሪካ ሀገራት ብቻ እንደነበሩ ይታወሳል።

የአፍሪካ ሀገራት ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው ምርቶች ላይ የቀረጥ ጭማሪ ሊያጋጥማቸው ይችላል በተባለባት በዚህ ወቅት፣ ቻይና ይህን ውሳኔ ማሳለፏ ለአፍሪካ ሀገራት አማራጭ የሚሰጥ እድል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን ነጻ ሀገር አድርጋ ዕውቅና በመስጠቷ ከዚህ እድል ተጠቃሚ እንደማትሆን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ቻይና ላለፉት 15 ዓመታት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛዋ የንግድ አጋር ሆና ቆይታለች፡፡

እ.አ.አ በ2023 ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ቻይና 170 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ተልከዋል።

ebc

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...