ቻይና የተማሪዎችን ጭንቀት ለመቀነስ የእንቅልፍና የስክሪን ጊዜ ገደብ ተጣለች

Date:

የቻይና መንግስት በሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚታየውን የተማሪዎችን ከፍተኛ የትምህርት ጫናና ተያያዥ የአእምሮ ጭንቀት ለመቀነስ ያለመ አዲስ ብሔራዊ መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል።

ይህ መመሪያ በዋነኝነት ተማሪዎች ረዘም ያለና ጥራት ያለው የእንቅልፍ ጊዜ እንዲያገኙ እንዲሁም የስክሪን አጠቃቀማቸው እንዲቀንስ ያሳስባል። በአዲሱ ሕግ መሠረት፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በየቀኑ ዝቅተኛው ዐሥር (10) ሰዓታት፣ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች ከዘጠኝ (9) ሰዓታት በታች፣ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ ቢያንስ ስምንት (8) ሰዓታት መተኛት አለባቸው።

የትምህርት ቤቶችና የወላጆች ኃላፊነት ደግሞ ተማሪዎች የመኝታ ሰዓታቸውን እንዲጠብቁ መርዳት ሲሆን፣ የአካባቢው የትምህርት ባለሥልጣናት ተማሪዎች የእንቅልፍ ጊዜያቸውን በሚቀንስ መልኩ የሚሰጡ የቤት ስራዎችን፣ የግል ትምህርቶችን እና በተለይም የቪዲዮ ጨዋታዎችን እንዲቀንሱ በጥብቅ አዟል።

በተለይ ደግሞ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት  ባለው ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት የቪዲዮ ጨዋታ አገልግሎት እንዳያገኙ ለማድረግ የቴክኒክ ሥርዓቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ መንግስት አስታውቋል።

ይህ ሁሉ እርምጃ የተወሰደው በቻይና ውስጥ የጤና ችግር እየሆነ የመጣውን የተማሪዎችን የእንቅልፍ እጦት በመቆጣጠር፣ አካላዊና አእምሯዊ ጤንነታቸውን በማሻሻል፣ ለጠንካራና ጤናማ ትውልድ ለመገንባት መሆኑን የቻይና የትምህርት ሚኒስቴር አስረድቷል።

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...