“አሜሪካ ተኩስ ከፈተችብኝ”ቬንዙዌላ

Date:


በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ተከታታይ ፍንዳታ  መሰማቱን ተከትሎ አዲስ ውጥረት ነገሰ።

ሰባት ፍንዳታዎች የተሰሙ ሲሆን አውሮፕላኖች ወደ ከተማዋ ዝቅ ብለው ከበረሩ በኋላ የሆነ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቬንዙዌላ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር ማዘዛቸውም ተሰምቷል።

የቬንዙዌላ መንግስት መግለጫ ያወጣ ሲሆን የትራምፕ አስተዳደር ቀጥተኛ ጦርነት ከፍቶብኛል ሲል ከሷል።

በካራካስ ላይ አውሮፕላኖች መብረራቸውን እና ፍንዳታ መኖሩን የአሜሪካ ባለስልጣናት እውቅናው አላቸውም ተብሏል።

በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ሲ ቢ ኤስ ይህን ያረጋገጠ ሲሆን ኒኮላስ ማዱሮ ላይ “መንግስታዊ ፍንቀላ ለማድረግ አደገኛው የአሜሪካ ጦር እርምጃ” እንደሆነም አስታውሷል።

የአሜሪካ መንግስት ካራካስ ላይ የአየር ጥቃት ፈፅሟል በሚል የማዱሮ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

በደቡባዊ ካራካስ በግዙፉ የጦር ሰፈር አቅራቢያ ዜጎች ከሀይል አቅርቦት ውጭ ሆነዋል።

ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተገናኘ ማዱሮን የሚከሱት ትራምፕ በምስራቃዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ እና ካሪቢያን ባህር ተደጋጋሚ ጥቃት ማስፈፀማቸው አይዘነጋም።

ዘገባው የቢቢሲ እና አልጀዚራ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...