የአሜሪካ መንግስት ለፕሬዚዳንት ትራምፕ መጓጓዣነት የሚውል ቦይንግ 747 ቅንጦት አውሮፕላን ከኳታር በስጦታ መልክ መረከቡን አስታውቋል ።
ታድያ ይሄ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው አውሮፕላን “የሚበር ቤተ መንግሥት” ተብሎ ተሰይሟል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ፔንታጎን ዋና ቃል አቀባይ ሲያን ፓርኔል በሰጡት መግለጫ “በሁሉም የፌደራል ህጎች እና መመሪያዎች መሰረት የኳታርን ስጦታ ተረክበናል” ብለዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚያጏጏዙበት አውሮፕላኑ ትክክለኛ የደኅንነት እርምጃዎችን እና የተግባር-ተልእኮ መስፈርቶችን ማሟላቱን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።
በተጨማሪም የአየር ሃይሉ ጸሐፊ የሆኑት ትሮይ ሜይንክ የሚያስፈልጉትን ለውጦች ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዳግም ማስተካከያውን ለማጠናቀቅ አመታትን ሊወስድ ብሎም 1 ቢሊዮን ዶላር ሊፈጅ የሚችል ሲሆን ይህም ከአውሮፕላኑ ዋጋ በእጥፍ ይበልጣል ሲል ኤን.ቢ.ሲ ኒውስ ዘግቧል።
