በአገራችን ውስጥ ውጤታማ እየሆኑ ከሚገኙ ሪልስቴቶች መካከል ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፈው ጃምቦ ሪልስቴት በሚዲያው ዘርፍ ጠንካራ ተዋናይ ከሆነው አርትስ ቴሌቪዥን የደረሰበት የሥራ ስምምነት ምሣሌያዊ አጋርነት መሆኑ ተነግሯል ::
በዚሁ አጋርነት አርትስ ቴሌቪዥን የዚህን ግዙፍ ተቋም የማስታወቂያ ሥራዎች ( Commercial Productions) የማኅበራዊ ሚዲያ ስልታዊ አተገባበርን ( Social Media Management) እንዲሁም ለተቋሙ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ “Marketing Collateral“ ግብዓቶችን ለመሥራት ከስምምነት ላይ በመድረስ የጃምቦ ሪልስቴት አምባሳደር የሆነው አንጋፋውና ተወዳጁ ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ በተገኘበት የስምምነት ውሉ ተፈፅሟል::
በስምምነቱ ወቅት የአርትስ ቴሌቪዥን እንዲሁም የጃምቦ ሪልስቴት የሥራ አስፈፃሚዎች የተገኙ ሲሆን የአርትስ ቴሌቪዥኑ ደረጀ ኃይሌም በብራንድ አምባሳደርነቱ በክብር እንግድነት ታድሟል::
