አትሌት ሱሌ ኡቱራ የፍትህ ጥሪ አቀረበች

Date:

አትሌት ሱሌ ኡቱራ ያለኝን ሀብት በፍርድ ተዛብቶ ተቀማሁ በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ገጿ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበች።

አትሌቷ ጉዳዩ ለረጅም ጊዜ እንደቆየና በስፖርት ሕይወቷ ላይም ተፅዕኖ እንዳሳደረ ገልጻለች። በጉዳዩ ላይ የተከሳሹን ወገን አስተያየት እስካሁን እንዳልሰማን የገለጸው ዘገባ፣ አግባብነት ያላቸው አካላት ጉዳዩን አጣርተው ፍትህ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

ሱሌ ኡቱራ ሀገሯን በስምንት ዓለም አቀፍ ውድድሮች ወክላ በጥቅሉ ሰባት ሜዳሊያዎችን እንዳስገኘች ዘገባው ያስታውሳል።

አትሌቷ ከእመቤት አንተነህ፣ ገነት አያሌው፣ ገንዘቤ ዲባባ እና መሰለች መልካሙ ጋር ባደረገቻቸው ውድድሮች ጠንካራ ተፎካካሪ እንደነበረችም ተጠቅሷል።

በመጨረሻም ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጉዳዩን እንዲመለከቱ ጥሪ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከድሬዳዋ እስከ ዱባይ የተዘረጋው የሌብነት ሰንሰለት፤ ተከሳሾቹ እስከ 14 ዓመት ከ4 ወር እስራት ተቀጡ

በድሬዳዋ ከተማ ከመኖሪያ ቤት የተለያዩ ዘመናዊ ሞባይል ስልኮችን በመስረቅ...

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከልና ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች ነው

ኢትዮጵያ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ...

አረንጓዴ አሻራ በተመድ ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ

ኢትዮጵያ ለኮፕ 32 አዘጋጅነት እንድትመረጥ አስተዋጽኦ ያደረጉት የአረንጓዴ አሻራ...

በሩሲያ ሳይቤሪያ የወታደራዊ ማጓጓዣ አውሮፕላን ተከስክሶ 19 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

በሩሲያ ደቡብ ምዕራብ ሳይቤሪያ በሚገኘው ኬሜሮቮ ግዛት የወታደራዊ ማጓጓዣ...