በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በተመለከተ በሶሻል ሚዲያ እና በፕሬስ የእርሳቸውን ያህል እየጻፈ ያለ ምሁር ያለ አይመስለኝም። አቶ ክቡር በንግዱ ውስጥ ካላቸው ተሳትፎ ባሻገር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እና ኮንፈረንሶች እየተጋበዙ ኢኮኖሚን፣ ልማትንና ቢዝነስን በተመለከተ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ እና ሌክቸሮችን በመጻፍ ከአንድ ምሁር የሚጠበቀውን ሀገራዊ ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ።
ዛሬ እርሳቸውንና የሚዲያ ሰዎችን አንድ ወሳኝ ነገር ልጠይቅ ነው። አቶ ክቡር የሚሰጡት ምሁራዊ ትንታኔ በኢንተርኔት ዓለም ብቻ ተገድቦ መቅረት የለበትም። ሰፊው ሕዝብ የትንታኔአቸው ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆን እና በኢኮኖሚና ቢዝነስ ዙሪያ ያለው ግንዛቤ እንዲጨምር ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል በአየር ላይ የሚቆይ የኢኮኖሚ talkshow መጀመር አለባቸው ብዬ አምናለሁ።
አቶ ክቡር የሚከፍቱት ቶክሾው format ምን መምሰል እንዳለበት በእርሳቸው የሚወሰን ነው። ሆኖም የTV ሰዎች ከእርሳቸው ጋር ተነጋግራችሁ ፕሮግራሙ እንዲከፈት ግፊት መፍጠር ያለባችሁ ይመስለኛል። ይህ ፕሮግራም ከተከፈተ ብዙኃኑ ተመልካች ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት ተሿሚዎች እና የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ጭምር ተጠቃሚ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ።
CC to
Kebour Ghenna Desta
አፈንዲ ሙተቂ
