የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ መዲናዋ ደረቅ ቆሻሻን በማስወገድ ከአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚ መሆኗን ዩ ኤን ሀቢታት ጥናት መረጋገጡን ገልጿል።
94 በመቶ የሚሆነውን ቆሻሻ ታስወግዳለች የተባለችው ከተማ በቀን ውስጥ ከ2500 እስከ 3000 ቶን ቆሻሻ እንደሚሰበሰብ ሰምተናል።
ቀድም ብሎ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም አቅም 2.5 በመቶ የነበረው ሲሆን ከአራት ዓመት ወዲህ 12 በመቶውን ጥቅም ላይ እየወላ ነው ትብሏል
ይህንነም የገንዘብ ምንጭ ማድረግ መቻሉን የአዲስአበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ገልፀዋል።
ያም ሆኖ አሁንም አብዛኛው የከተማ ቆሻሻ ጥቅም ላይ እየዋለ ባለመሆኑ ይበልጥ መጠቀም የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።
የከተማው ኗሪው ውበትና ፅዳት ላይ ለውጥ እያሳየ ነው የተበለ ሲሆን በዚያው ልክ ግን ከተማዋን የሚያቆሽሹና የሚያበላሹ አካላት መኖሯቸው ተገልጿል።
የሚፈለገውን ግንዛቤ ለመፍጠር ውብ፣ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን ለመፍጠር የሚዲያ ሚና ይበለጥ እንዲጠናከር ለጋዜጠኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
