አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ስሜን ቀይሬያለሁ ብሏል

Date:

ባንኩ ለ14 ዓመታት ሲጠራበት የነበረውን ስያሜ ወደ አዲስ ባንክ መቀየሩን አስታውቋል።

በተጨማሪም የባንኩን አርማም መለወጡን ገልጿል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኃይሉ ዓለሙ፤ ባንኩ ከሰራተኛ ማህበራት ጀምሮ እስከ ዕድር ድረስ ባሉ ማህበራት የተቋቋመ መሆኑን አንስተዋል።

የግለሰቦች ድርሻ 35 በመቶ መሆኑንም ነው የገለፁት።

ባንኩ ከ17 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉትም ተነስቷል።

ባንኩ አገልግሎቱ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ሁሉንም አካታች ያደረገ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በዚህም መታወቂያ ለሌላቸው እና አገልግሎቱን ማግኘት ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች በአሻራ ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጿል።

አዲስ ባንክ ተቀማጭ ሂሳቡ ማደጉን እንዲሁም ከፍተኛ ትርፍ ማግኘቱን ገልፆ፤ በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን የዝቅተኛ ካፒታል መጠን ማሟላት መቻሉንም አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...