ኢራን ከአሜሪካ ጋር የሚደረግን ውይይት ውድቅ ማድረጓ ጥልቅ አለመተማመን እንዳለ ያሳያል

Date:

ዋሺንግተን ንግግር እየተደረገ መሆኑን ስትገልጽ ቴህራን በበኩሏ ወዲያውኑ ውድቅ አድርጋለቸ። ይህ አለመግባባት የሚያሳየው ሁለቱ አገራት ከዚህ በፊት ባደረጓቸው ድርድሮች ወቅት የተፈጠረን ጥልቅ አለመተማማን ነው።

ከዚህ ቀደም በሁለቱ አገራት መካከል ሁለት ጊዜ ውጥረትን ያረግባሉ የተባሉ ንግግሮች ተጀምረው ነበር።

ነገር ግን ሁለቱም ንግግሮቹ በሂደት ላይ እያሉ አሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከፍተውባታል።

ከኢራን አንጻረ ንግግር መጀመር ጦርነት ይከፈታል የሚለውን ዕድል አይቀንሰውም።

እንዲያውም ጦርነቶቹ የተጀመሩት ንግግሮቹ እየተካሄዱ ባለበት ወቅት ነው። ለዚህም ነው የትራምፕ ንግግር በጥርጣሬ የታየው።

ነገር ግን የኢራን ማስታባበያም ቢሆን እውነታውን አያሳይም። ከመጋረጃ ጀርባ በርካታ ነገሮች የተከናወኑ ነው።

ዲፕሎማሲን የሚደግፉ ባለሥልጣናት ሳይቀር ጫና ውስጥ ናቸው። በድጋሚ ድርድር መጀመር አደገኛ ሊሆን ይችላል።

አሁን የሚደረግ ድርደር ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት የተለየ የሚሆንበትን መንገድ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም። ለዚህም ነው የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባሰ አራጋቺን ጨምሮ ሊሎች የአገሪቱ ባለሥልጣናት ጠንካራ ድምጸት ባለው ቃል ንግግርን ውድቅ የሚያደርጉት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

30 ሺህ ተሳታፊዎችን የሚያስተናግደው ዓለማ አቀፍ የጤና ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የዲፕሎማሲ መዲናዋ አዲስ አበባ 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ...

የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነዉ

የትምህርት ጥራቱን የበለጠ ለማሻሻል የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ...

የፊንቴክ ሥራ አስኪያጅ በከባድ የማታለል ወንጀል ተከሰሰ

​በአዲስ አበባ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስ፣...

ኢራን በሆርሙዝ በኩል ሊያልፉ የነበሩ ሦስት መርከቦችን መመለሷን አሳወቀች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ጠዋት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል...